እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

8 - ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ የተባረክሽ ነሽ ይሉኛል

8

‹‹ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ የተባረክሽ ነሽ ይሉኛል››

የእግዚአብሔር ቃል፤- የቅድስት ድንግል ማርያም የምስጋና ጸሎት፤ ሉቃስ 1፡ 46-55

የምስጋና ጸሎት፣ በአዲስ ኪዳን ስለ እናታችን ማርያም እንደሌላው ታሪክ ሁሉ፣ የመጀመሪያ ክርስቲያኖች በማርያም ላይ ያላቸውን እምነት ይመሰክራል፡፡ ማርያም በሐዋርያት ጊዜ ማን ነበረች? እነርሱ፣ ማርያምን እንዴት ይጠሩ፣ ያስታውሱና ያመሰግኑ ነበር? የዚህን ጥያቄን መልስ አዲስ ኪዳንን በማንበብ እናገኛለን ምክንያቱም ወንጌላውያንና ሌሎች ያመኑትንና ለእምነታችን ይጠቅማል ብሎ ያሰቡትን ብቻ ጽፈዋል፤

‹‹ ›› (ዩሐ 20፡ 31)

ማዕከሉ ሁል ጊዜ ክርስቶስ ነው፡፡ በድህንነት ታሪክ፣ በኢየሱስ ተልእኮና በቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ የማርያም ሚና ማወቅ፣ ስለ ኢየሱስና ስለ ወንጌሉ የበለጠ እንድንረዳ ይረዳናል፡፡

በአዲስ ኪዳን እናታችን ማርያም፤

  • ድንግል ናት (ሉቃ 1፡ 27፤ ንጽ. ኢሳ 7፡ 14)
  • የተወደደች፣ የተባረከች፣ የተመረጠች፣ ጸጋን የተሞላች፣ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ ያገኘች ናት (ሉቃ 1፡ 28-30)፡፡ እነዚህ ስያሜዎች ለማርያም እንደ ስም ነው የሚጠቅሙ፡፡ ስለዚህም አስፈላጊውን ነሕልውናዋን ባህሪ ይገልጻሉ፡፡ ሕይወቷን ሙሉ በእግዚአብሔር የተወደደችና በጸጋው የተሞላች ናት፡፡
  • የእግዚአብሔር እናት ናት፤

‹‹ ›› (ሉቃ 1፡ 31-32)፡፡

‹‹ ›› (ሉቃ 1፡ 43)፡፡

  • በመንፈስ ቅዱስ የተሞላች ናት፤

‹‹ ›› (ሉቃ 1፡ 35)፡፡ እናታችን ማንፈስ ቅዱስ ከኤልሣቤጥ ጋር ተካፈለች፤

‹‹ ›› (ሉቃ 1፡ 41)፡፡ መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ በወረደ ጊዜ እናታችን ማርያም ከሐዋርያትና ከመጀመሪያ አማኞች ጋር ትጸልይ ነበር (ንጽ. ሐ.ሥራ 1፡ 14፤ 2፡ 1-5)፡፡

  • የእግዚአብሔር አገልጋይ ፈቃዱን ለመፈጸምና በእግዚአብሔር የድህንነት ዕቅድ ለመተባበር ዝግጁ ናት፤

‹‹ ›› (ሉቃ 1፡ 38)፡፡ እመቤታችን የመጀመርያና ምሳሌ የምትሆን የክርስቶስ ተከታይ ናት ምክንያቱም እርሷ የእግዚአብሔርን ቃል ተቀበለች፤ አዳምጣም በሥራ ላይ አዋለች፡፡ እርሷ ክርስቶስን ለመከተል ለሚፈልጉ ሁሉ አርአያ ናት፡፡

  • በጣም የተባረከች ናት፤

ማርያም የብጽእናን ሕይወት ስለኖረች (በመንፈስ ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉ፣ የዋሆች፣ ምህረትን የሚያደርጉ፣ ንጹሕ ልብ ያላቸው፣ እርቅና ሰላምን የሚያደርጉ፣ ስለጽድቅ ስደትና መከራን የሚቀበሉ … (ንጽ. ማትዎስ 5፡ 1-12) እርሷ የእምነትና የክርስቶስ ፍጹም ተከታይ ምሳሌ ናት፡፡

እመቤታችንን እያከበርንና እግዚአብሔርን በእናቱ ባደረገው አስደናቂ ነገሮች እያመሰገንን፣ በሕይወታችንና በቤተሰባችን እግዚአብሔር ላደረገው አስደናቂ ነገር በጥልቀት ማሰብ እንችላለን፡፡ በቤተሰባችን የእግዚብሔርን ሕልውና እንገነዘባለን?

በእስራኤላዊያንና በማርያም ታሪክ ውስጥ የሰራው አመላክ አሁንም በእኛ ሕይወት ውስጥ ለመስራት ይፈልጋል፡፡

እስራኤላዊያንና ማርያም እግዚአብሔርን በሕይወታቸው መኖሩን ስለተረዱ፣ ታሪካቸውን ወደ ደኅንነት ታሪክ ለውጠዋል፡፡

እኛም የእግዚአብሔር ሥራ በሕይወታችንና በቤተሰባችን ውስጥ ማየት ከቻልን፣ ታሪካችንን ወደ ደኅንነት ታሪክ መለወጥ እንችላለን፡፡

እንጸልይ፡-

የፍቅርና የምህረት አምላክ ሆይ፣ በመልአኩ መልእክት ቅድስት ድንግል ማርያም ልጅህን ተቀበለችና በመንፈስ ቅዱስህ ብርሃን ተሞላች፣ የቃልህ ቤተ መቅደስ ሆነች ሁል ጊዜ ፈቃድህን ለመፈጸም ዝግጁ የሆነችውን የቅድስት ድንግል ማርያምን ምሳሌነት ለመከተል እርዳን፡፡ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንለምንሃለን፡፡ አሜን፡፡

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት