እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ይህ ክፍል አጠር ባለ መልኩ በሰንበት ወንጌሎች ላይ የሚደረጉ አስተንትኖዎች የሚሰባሰቡ በት ነው።

Display # 
< < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < <
Title Author Hits
የመቶ አለቃው እምነት - (ማቴ. 8፡5-13) ዘክረምት 3ኛ Written by Super User 3843
ታማኙና መልካሙ አገልጋይ - ዘገብር ኄር Written by Super User 1238
ዘምኩራብ፣ ዘመፃጉእ፣ ዘደብረ ዘይት፣ ዘገብር ኄር Written by Super User 12004
አዎን ለነፃነት ተጠርተናል! ዘመፃጒዕ Written by Super User 4257
እግዚአብሔር በልጁ ልደት ሳመን! - ዘልደት Written by Super User 7336
“የሁላችን አጥናኝ መንፈስ ጰራቅሊጦስ የተመሰገነ ይሁን!” Written by Super User 10833
4ኛ ሰንበት ዘአስተምህሮ 2005 ዓ.ም. ሰንበት ዘመጻጕዕ Written by Super User 2250
የእግዚአብሔርን ቃል የሚያዳምጥ ጆሮ - ቅድስት ቤተሰብ -ዘጥምቀት ፪ኛ Written by Super User 2635
በሥጋ ልጇ ከመሆኑ በፊት የእምነቷ ልጅ ነው! Written by Super User 3809
ሁላችሁ የእግዚአብሔር ልጆች በሥራችሁ አሜን በሉ! ዘልደት Written by Super User 2514
ዘኖላዊ Written by Super User 5205
ዘኒቆዲሞስ - ከእኔነት ቅርፊታችን መውጣት Written by Super User 4275
ዘጥምቀት - አስተር እዮ 2ኛ Written by Super User 4209
ዘጥምቀት - አስተርእዮ 2ኛ Written by Super User 5509
ዘስብከት 2ኛ - ዘብርሃን Written by Super User 5194
ዘስብከት 1ኛ Written by Super User 4330
ዘአስተምሕሮ 5ኛ Written by Super User 3928
ዘአስተምሕሮ 4ኛ- ዘመፃጉዕ Written by Super User 3824
ዘአስተምሕሮ 3ኛ Written by Super User 4807
ዘአስተምሕሮ 2ኛ Written by Super User 3922
ዘአስተምሕሮ 1ኛ Written by Super User 4272
ዘጽጌ 3 Written by Super User 6141
ዘጽጌ 3 Written by Super User 3966
ዘክረምት10ኛ Written by Super User 3457
ዘክረምት 9ኛ Written by Super User 4302
2ኛ ፍልሰታ Written by Super User 4295
ፍልሰታ ማርያም 1ኛ Written by Super User 5949
ዘገብር ኄር Written by Super User 4377
ዘትንሣኤ Written by Super User 4949
ዘክረምት Written by Super User 3965
ዘጰራቅሊጦስ Written by Super User 12353
ዘደብረ ዘይት Written by Super User 11249
ዘወረደ Written by Super User 13432
ዘጥምቀት Written by Super User 15836
ዘጽጌ 5ኛ Written by Super User 15499
ዘጽጌ 4ኛ Written by Super User 21436
ዘፍሬ Written by Super User 11487
ዘዮሐንስ (አዲስ ዓመት) Written by Super User 20719
ዘክረምት 2ኛ Written by Super User 2775
3ኛ ጰራቅሊጦስ Written by Super User 25407
2ኛ ጰራቅሊጦስ Written by Super User 24693
ዘጰራቅሊጦስ Written by Super User 25126
ዘዕርገት Written by Super User 8558
ዘክረምት 2ኛ - ጴጥሮስ ወጳውሎስ Written by Super User 23897

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት