እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

9- እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፤ የአዲስ ኪዳን ታቦትና እውነተኛ አማኝ ናት

9

እመቤታችን ቅድስ ድንግል ማርያም፤ የአዲስ ኪዳን ታቦትና እውነተኛ አማኝ ናት፡፡

የቃል ኪዳን ታቦት

እግዚአብሔር በሲና ተራራ በድንጋይ ጽላቶች የተጻፈውን ትእዛዛት ለሙሴ የሰጠውንና ሕዝቡ በበረሃ እየተጓዙ እያሉ የሰጣቸውን መና የያዘ ነው፡፡ ታቦቱ እግዚአብሔር በሕዝቡ መካከል ስላለው ንቁና ተወዳጅ ሕልውና ምልክት ነበር፤

‹‹ ›› (ዘሌ 26፡ 11)

ደመና በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደሱን እንደሸፈነ

የመንፈስ ቅዱስ ጥላ እናታችን ቅ. ድንግል ማርያምን ሽፈነ፡፡

1 መጸሐፈ ነገሥት 8፡ 10-12

ሉቃስ 1፡ 35

‹‹ካህናቱ ከቤተ መቅደሱ እንደወጡ ቤተ መቅደሱ ድንገት በደመና ተሞላ፤ በደመናውም ውስጥ የእግዚአብሔር የክብር መገለጥ ብርሃን ያንጸባርቅ ስለነበር ካህናቱ ተመልሰው ለመግባትና አገልግሎታቸውን ለማከናወን አልቻሉም፡፡ በዚህ ጊዜ ሰሎሞን እንዲህ ሲል ጸለየ፤ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ አንተ በደማናና በጨለማ ውስጥ መሰወርን ወድደሃል፡፡››

መልአኩም እንዲህ ሲል መለሰ፤ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑል እግዚአብሔርም ኀይል በአንቺ ላይ ይሆናል፤ ስለዚህ ከአንቺ የሚወለደው ሕፃን ቅዱስ ነው፤ የእግዚአብሔርም ልጅ ይባላል፡፡››

ወንጌላዊው ሉቃስ ማርያም ኤልሳቤጥን ለመጎብኘት ያደረገችውን ጉዞ (ሉቃ 1፡ 39-45) የቃል ኪዳኑ ታቦት ከይሁዳ ወደ ኢየሩሳሌም የመወሰዱ ጉዞ (ንጽ. 2 መጺሐፈ ሳሙኤል 6፡ 1-23) ጋር ያነፃጽራል፡፡ በዚህ ምክንያት እኛ ቅድስት ድንግል ማርያምን ‹‹የአዲስ ኪዳን ታቦት›› ብለን እንጠራታለን፡፡

2 መጸሐፈ ሳሙኤል 6፡ 1-23

ሉቃስ 1፡ 39-45

በብሉይ ኪዳን ታቦት ውስጥ እገዚአብሔር ለሙሴ ተሰጠው የእግዚአብሔር ቃል ነበር፡፡

በማርያ የእገዚአብሔር ቃል ሥጋ ሆነ፡፡

ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩ እስራኤላውያን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ሊያመጡ በይሁዳ ወደሚገኘው ወደ በዓላ ሄዱ፡፡

ማርያም በተራራማው በይሁዳ አገር ወዳለችው ከተማ በፍጥነት ተነሥታ ሄደች፡፡

ደዊትና እስራኤለውያን በሙሉ ኀይላቸው በመዘመር በእግዚአብሔር ፊት ደሰት አደረጉ፡፡

ኤልሳቤጥ የማርያምን የሰላምታ ቃል በሰማች ጊዜ በማሕፀንዋ የነበረው ህፃን ዘለለ፡፡ ኤልሳቤጥም ድምፅዋን ከፍ አድርጋ ተናገረች፡፡

እግዚአብሔር በቁጣ ተነሳስቶ ዑዛን በመግደሉ ዳዊት እግዚአብሔርን ሰለፈራ ‹‹እንዲህ ከሆነማ የቃል ኪዳኑን ታቦት እንዴት ልወስደው እችላለሁ?›› አለ

ኤልሳቤጥ እንዲህ አለች፤ ‹‹የጌታዬ እናት ልትጎበኘኝ መምጣትዋ ለኔ እንዴት ያለ ታላቅ ክብር ነው!

የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት የዖቤድኤዶም ቤት ሦስት ወር ተቀመጠ፤ እግዚአብሔርም ዖቤድኤዶምንና ቤተሰቡን ባረከ፡፡

እናታችን ማርያም ከኤልሳቤጥ ጋር ሦስት ወር የህል ከቆየች በኋላ ወደ ቤትዋ ተመልሳ ሄደች፡፡

እናታችን ማርያም ስላመነች ተባረከች

ኢየሱስ፤ ‹‹ ›› (ሉቃ 11፡ 28)

በዚህ ንግግሩ ኢየሱስ እናቱን ዝቅ አድርጎል ማለት ነው ወይ? በዚህ ንግግሩ ኢየሱስ የእናቱን እውነተኛ ታላቅነት ለመግለፅ ይፈልጋል፡፡ እርሷ በመጀመሪያ አምና የእግዚአብሔርን ቃል ተቀብላ በተግባር ላይ አዋለች፡፡

ማርያም የተባረከችና የኢየሱስ እናት የሆነችው ኢየሱስን ስለጸነሰች ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር ያለውን ስላመነችና የሰማዩን አባት ፍቃድም ስለፈጸመች ነው፤ ‹‹አንቺ እግዚአብሔር የተናገረውን ሁሉ የሚፈጽም መሆኑን በማመንሽ ምንኛ የታደልሽ ነሽ››፡፡

ማርያም የመጀመሪያዋ ኢየሱስን የተቀበለች ስትሆን ‹‹እነሆ እኔ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነኝ፤ አንተ እንዳልህ ይሁንልኝ›› በማለት በእሽታና በትህትና መልስ ሰጠችው፡፡

በቤተሰባችን ውስጥ ተስፋ ሊጠፋ በሚጣጣርበት ጊዜ፤ በመስቀሉ ሥር እንኳን በእምነት ጸንታ የቆመችውን ማርያምን ማየት አለብን፡፡ ተስፋዋ በሰዎች ዘንድ በተጠላና በተከዳ ልጇ ላይ ነበር፡፡ በችግሮቻችን መኃል እንኳን የእግዚአብሔርን ፍቅርና የእግዚአብሔርን እውነተኛ ፊቱን ማግኘት እንድንችል እንድትረዳን ማርያምን እንለምናት፡፡

እንጸልይ፡-

አባት ሆይ፣ አንተ የድንግል ማርያምን ልብ ለመንፈስ ቅዱስህ ምቹ መኖርያ ቤት እንድትሆን አዘጋደኃት፡፡በእርሷ ጸሎት እኛም ለክብርህ ብቁ መኖርያ እንድንሆን ታደርገን ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንለምንሃለን፡፡ አሜን፡፡

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት