እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

7- እግዚአብሔር ታላላቅ ገዥዎችን ከዙፋናቸው አውርዶአቸዋል

7

እግዚአብሔር ታላላቅ ገዥዎችን ከዙፋናቸው አውርዶአቸዋል

የእግዚአብሔር ቃል፤ - የቅድስት ድንግል ማርያም የምስጋና ጸሎት፤ ሉቃ 1፡ 46-55

‹‹እግዚአብሔር ለሚፈሩት ሰዎች ሁሉ ከትውልድ እስከ ትውልድ ምሕረቱን ያደርጋል፡፡ ታላላቅ ገዥዎችን ከዙፋናቸው አውርዶአቸዋል፤ ዝቅተኞችን ግን በክብር ከፍ አድርጎአቸዋል››፡፡

እመቤታችን የእግዚአብሔር ጥበብ ምስክር ናት፡፡ እግዚአብሔር እንደ ዓለም አያስብም አይመርጥም፡፡ እርሱ ከዝቅተኞች፣ በመንፈስ ድሆች ከሆኑትና ከትሁታን ጋር ነው፡፡

ቤተሰቦቻችንና ብዙ ዝቅተኞች ሰዎች ለመኖር ሲሉ ጨቋኝ ሰዎችን መዋጋት አለባቸው፡፡ ብዙዎቻችን  እንደ እነዚህ ጨቋኝ ሰዎች ለመሆን ሥልጣን፣ ገንዘብና ክብር እየተፈታተነን ነው፡፡ ሌሎችን በመጥፎ ድርጊታቸው የሚውቅሱ ሰዎች እነርሱ፣ ስልጣን ካገኙ ወይም ሀብታመ ከሆኑ በኋላ፣ እነርሱ እራሳቸው እንደነዚህ ሰዎች ወይም ከእነርሱ የባሱ ይሆናሉ፡፡ ብዙ ሰዎች ድሆችንና የተጨቆኑትን በመርሳት ሰፊ የዓለምን መንገድ ይመርጣሉ፡፡

መዝሙረ ዳዊት ለዕብራውያንና ለክርስቲያኖች የዕለት ጸሎታቸው ነው፡፡ በዚህ ጸሎት አማኞች እምነታቸውን፣ ተስፋቸውን፣ ጭንቃቸውን፣ ሥቃያቸውን፣ ፍርሃታቸውን፣ ቅሬታቸውን፣ ምስጋናቸውን፣ ውዳሴአቸውን፣ ደስታቸውንና ፍቅራቸውን ይገልጻሉ፡፡ ዛሬ በመዝሙረ ዳዊት 10፡ 1-18 እንጸልያለን፡፡ ይህ መዝሙር ትዕገሥት ያጡ ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ በመተማመን ያቀረቡ የድሆችና የተጨቆኑት ሁኔታውን እንዲለውጥ የቀረበ ጸሎተ ነው፡፡ በዚህ ጸሎት ውስጥ ብዙ ለእገዚአብሔር የምናቀርብ ጥያቄዎቻችንና የተለያዩ የእብራት ሐሳቦቻችንን ልናገኝ እንችላለን፡፡

እገዚአብሔር ሆይ ስልምን እንደዚህ ራቅህ? በችግር ጌዜስ ስለምን ትሰወራለህ?

ክፉ ሰዎች ይታበያሉ፤ ድኾችንም ያሳድዳሉ፤ ለሌሎች ባጠመዱት ወጥመድ ራሳቸው ይግቡበት፡፡

ኃጢአተኛ በክፉ ምኞቱ ይመካል ስግብግብ ሰውም ይራገማል፤ እግዚአብሔርንም ይክዳል፡፡

ኃጢአተኛ ስለ እግዚአብሔር ግድ የለውም፤ በትዕቢቱም ‹‹እግዚአብሔር የለም›› ብሎ ያስባል፡፡

ንጽሖችን ሰዎች በስውር ለመግደል በየመንደሩ ያደፍጣል፤

ምስኪኖችንም ለማጥመድ አትኩሮ ያያል፡፡

. . . . .

ኃጢአተኛም በአሳቡ ‹‹እግዚአብሔር እኔን ምንም አያደርገኝም፤ ዐይኖቹን ጨፍኖአል ከቶም አያየኝም›› ይላል፡፡

እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥ እነዚያን ክፉ ሰዎች ቅጣቸው፤ የተጨቆኑትን አስታውሳቸው፡፡

ኃጢአተኛ ሰው እግዚአብሔርን ስለምን ይንቃል? አሳቡስ ‹‹እግዚአብሔር አይቀጣኝም›› ለምን ይላል?

ይህም ሆኖ ሁሉ ነገር ይሳካለታል፤ ትዕቢተኛም ስለሆነና የእግዚአብሔር ሕግ ከእርሱ አስተሳሰብ የራቀ ስለሆነ ሊያስተውለው አይችልም

በጠላቶቹም ላይ ያፌዛል፡፡

‹‹እኔ ከቶ አልዋረድም ችግርም ሳይደርስብኝ እኖራለሁ›› ብሎ ያስባል፤ ንገግሩም በእርግማን፤ በሐሰትና በዛቻ የተሞላ ነው፤ በተንኮልና በክፋት የተማሉ ቃላትን ለመናገር ይቸኩላል፡፡

አንተ ግን በእርግጥ ታያለህ፤

ችግርንና ሥቃይን ትመለከታለህ፤

ሁል ጊዜም ለመርዳት ዝግጁ ነህ፤

አንተ አባትና እናት የሌላቸውን ልጆች ዘወትር ስለምትረዳ ምስኪኖች ሁሉ እንድትረዳቸው ወደ አንተ ይቀርባሉ፡፡

. . . . .

እግዚአብሔር ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ ይኖራል…

እግዚአብሔር ሆይ!

አንተ የምስኪኖችን ጸሎት ትሰማለህ፤

ታበረታታቸዋለህ፤

የጭቁኖችንና አባትና እናት የሌላቸውን ልጆች ጩኸት ትሰማለህ፤ ለእነርሱመ ትፈርድላቸዋለህ፤ ሰለዚህ ከአፈር የተፈጠሩ ከንቱ የሆኑ ሰዎች ከእንግዲህ ወዲህ አያስጨንቁአቸውም፡፡

እናታችን ማርያም ዝቅተኛ ሆና ሳለች ከእግዚአብሔር ዘንድ ክብር አገኘች፣ እና እርሷ በታዝዞዋና ለድህንነት ዕቅድ ባደረገችው ትብብር፣ ወደ ነፃነታችን የሚወስድ በር ክፈተችልን፡፡

በእግዚአብሔርና በኃጢአት መካከል ያለው ውጊያ እየቀጠለ ነው፡፡ በየትኛው ጎን ነው የቆምነው? ንጹሕ ልብ ያላቸውና እንደ እግዚአብሔር የሚያስቡ፣ እንደ ማርያም ያሉ ሰዎች ብቻ በዚህ ዓለም ላይ አዲስ ነገር ደህንነትን፣ ፍቅርን፣ ፍትህን ሊያመጡ ይችላሉ፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ በኢ-ፍትሐውያን ፍርድ ቢሰጢውም የዓለም ፈራጅ እንደሆነ ዛሬም የተጨቁኑት ወደፊት በእግዚአብሔር ፈቃድ ፈራጃችን ይሆናል፡፡

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት