እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ሰባቱ ልመናዎች

ሰባቱ ልመናዎች

/የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ከቁጥር 28ዐ3-28ዐ6/

እግዚአብሔርን ለማምለክ ለመውደድና ለመባረክ ራሳችንን ከእርሱ ፊት ካቀረብን በኋላ ልጅነትን ያስገኘልን መንፈስ ሰባት ልመናዎችና ሰባት ቡራኬዎችን በልባችን ውስጥ ያጭራል፡፡ ከሰባቱ መካከል በይበልጥ ነገረ መለኮታዊ የሆኑት የመጀመሪያዎቹ ልመናዎች ወደ አብ ክብር ይስበናል፤ የተቀሩት አራቱ ደግሞ ወደ እርሱ የሚወስዱ መንገዶች እንደመሆናቸው ጭንቀታችን ለጸጋው ያቀርባሉ፡፡ ‹‹በፏፏቴህ ድምፅ ቀላይ ቀላይን ትጠራታለች›› መዝ. 42፡7

የመጀመሪያዎቹ ልመናዎች “ስምህ፣ መንግስትህ፣ ፈቃድህ” ስለ እርሱ ወደ እርሱ ይመሩናል፡፡ ከሁሉ አስቀድሞ ስለምንወደው ነገር ማሰብ የፍቅር ባሕሪ ነው፡፡ በሦስቱም ልመናዎች እኛን የሚመለከት አንዳችም ነገር አንጠቅስም፡፡ ተወዳጁ ልጅ ስለ አባቱ ክብር የለው የሚያንገበግብ ፍላጐት እንዲያም ሲል ጭንቀት ይመስጠናል፡፡ “ስምህ ይቀደስ፣ መንግስትህ ትምጣ … ፍቃድህ … ይሁን” እነዚህ ሦስቱ ልመናዎች በክርስቶስ የማዳን መስዋዕት ምላሽ አግኝተዋል፤ ሆኖም ከዚያ ወዲህ እግዚአብሔር ገና ሁሉ በሁሉ አልሆነምንና በተስፋ ወደ መጨረሻው ፍጻሜያቸው  እያመሩ ነው፡፡

ሁለተኛዎቹ የልመና ዝርዝሮች እንደ አንዳንዶቹ ቁርባናዊ የምልጃ ጸሎቶች በተመሳሳይ እንቅስቃሴ ይገለፃሉ፡፡ የምሕረቶች አባት ዓይኖች አሽቆልቁለው ወደ እኛ እንዲያተኩሩ ለእርሱ የምናቀርበው የተስፋዎቻችን መባእ ሆነው ይቀርባሉ፡፡ “ስጠን … ይቅርበለን … ወደ … አታግባን … አድነን…” የሚሉት ልመናዎች ከእኛ ወደ ላይ ይሄዳሉ፤ የእኛንም ከዚህ ጊዜ አንስቶ በአሁኑ ዓለማችን የሚመለከቱን ይሆናሉ፡፡ አራተኛውና አምስተኛው ልመናዎች ምግብ ማግኘታችንና ከኃጢአት መፈወሳችን … በጠቅላላ ሕይወታችንን የሚመለከቱ ናቸው፡፡ የመጨረሻዎቹ ሁለት ልመናዎች ለሕይወት ድል የምናደርገውን ፍልሚያ የጸሎት ውጊያ የሚመለከቱ ናቸው፡፡

በመጀመሪያዎቹ ሦስት ልመናዎች አማካይነት በእምነት እንጐለብታለን፤ በተስፋ እንሞላለን፣ በፍቅርም እንቃጠላለን፡፡ ፍጡራንና ኃጢአተኞች በመሆናችን ከዓለምና ከታሪክ ጋር ለተሳሰረውና ለወሰን የለሹ የእግዚአብሔር ፍቅር ለምናቀርበው በዚያ “ለእኛ” መለመን አለብን፤ ምክንያቱም አባታችን የማዳን እቅዱን ለእኛና ለመላው ዓለም ወደ ፍጻሜ የሚያደርሰው በክርስቶስ ስምና በመንፈሱ ኃይል ነውና፡፡

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት