እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የእግዚአብሔርን መንገድ አዘጋጁ

የእግዚአብሔርን መንገድ አዘጋጁ

ብዙ ዘመናት አስቀድሞ ኢሳያስ መሢሕ መድኃኒት ከመምጣቱ በፊት መልእክተኛ እንደሚመጣ ትንቢት ተናግሮ ነበር፡፡ ትንቢቱ እንዲፈጸም ክርስቶስ ያ ደኀንነት ከመጀመሩ በፊት የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ አባት ዘካርያስ  በትንቢት ተናግሮ እንደነበር እግዚአብሔር ለእስራኤል ልጆች ኢየሱስን መድኃኒታቸውን እንደቀበሉ ሰበከላቸው፡፡  የእግዚአብሔር መንግስት ቀርቦአልና ስንሐ ግቡ እያለ በበረሃ የሚጮህ የአዋጅ ቃል ለእግዚአብሔር የሚሆን መንገድ አዘጋጁ፣ መንገዶቹ አቅኑ፣ ጉድጓዶች ይሞሉ፣ ተራራና ኮረብታ ሁሉ ዝቅ ይበል፣ ዳገትና ቁልቁለቱ ሜዳ ይሁን፣ ወጣገባው መሬት ይደልደል፣ የእግዚአብሔር ክብር ሊገለጥ ነውና፡፡John_the_Baptist

ከእግዚአብሔር የሚመጣ ሁሉ በነፍስ ወከፍ ደኅንነት ያገኛል፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ተናግሮአል በማለት የኢሳይያስን ትንቢት እየጠቀሰ ለአይሁዳውያን የኢየሱስን መምጣት አስታወቃቸው፡፡ ሊያድናችሁ ከሰማይ የሚመጣውን መሢሕ በልባቸው አምነው እንዲቀበሉ መከራቸው፡፡ ከዓመት ዓመት ከዘመን ዘመን ቤተክርስቲያን ለእኛም የእግዚአብሔርን መንገድ አሰናዱ ጥረጉ የሚለውን የመጥምቁ ዮሐንስን አዋጅ አድጋሚ ትነግረናለች፡፡ እንዴት አድርገን ነው የምናዘጋጀው? ቅዱስ ዮሐንስ “ንስሐ ግቡ” እንዳለን ንስሐ ገብተን የእግዚአብሔርን መንገድ እናዘጋጅ፡፡

ሕፃኑ ኢየሱስ ወደ እኛ የሚመጣበትን መንገድ ልናዘጋጅ እርሱ የሚጠላውን የሚከለክለውን የኃጢአትን መንገድ ትተን የሚወደውንና ተደስቶ ወደ እኛ እንደመጣ የሚያደርገውን የጽድቅ መንገድ እንድንይዘ ያስፈልገናል፡፡ ወደ እኛ እንዳይመጣ የሚከለክል የኃጢአት ተራራ ጥል፣ ቅንዓት፣ ሁከት፣ ዝሙት፣ ቂም በንስሐ መደምሰስ አለብን፡፡ በውስጣችን የሚገኝ የመንፈስ ቅዝቃዜ የመንፈሳዊነት ጉድለት በጸሎት በተጋድሎ በበጐ ሥራ በትሕትና በፍቅር በየዋሕነት በምሕረት በትዕግስት በሃይማኖት በእምነት እንድንሞላው ያስፈልገናል፡፡ ጠመዝማዛ አሰተሳሰብና አረማመድ እንዲቀና ንግግራችንና ሥራችን የታረመ እንዲሆን ሕይወታችን በሙሉ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር እንዲስማማ አድርገን መዘጋጀት አለብን፡፡

እንደዚህ ያለ መንገድ ከጠረግን ሕፃን ኢየሱስ ተደስቶ ወደ እኛ በመምጣት ወደ ልባችን ይገባል፡፡ መለኮታዊውን ሕፃን በመንፈስ ንጹሐን ሆነን ተዘጋጅተን ከአገኘነው በኋላ በመንፈስ እንደገና እንደምንወለድ የልደቱን ጸጋ ያድለናል፡፡

ልደት ለነፍሳችን እንጂ ሥጋችንን እንዲጠቅም የተዘጋጀ አይደለም፡፡  ልደት በሥጋ የምንደሰትበት የምንጠጣበት የምንለብስበት በነፍስ ግን ተርበን ተጠምተን በጸጋ ራቁታችን የምንወጣበት የምንውልበትና ነፍሳችን የምትጐዳበት የምታዝንበት ቀን  ሊሆን አይገባም፡፡ ልደት የነፍስ በዓል ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ቀን ነፍሳችን በጸጋና በመንፈሳዊ ደስታ መሞላት አለበት፡፡ ይህን እንድናገኝ ደግሞ አስቀድመን በሚገባ ልንዘጋጅ ያስፈልጋል፡፡


ምንጭ፡- መንፈሳዊ ማሳሰቢያ

እህት እሌኒ ይሁኔ - ኦረሶላይን እህቶች- አዲስ አበባ

 

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት