እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

3. መጽሐፍ ቅዱስን ማን ጻፈው?

3. መጽሐፍ ቅዱስን ማን ጻፈው?

በርግጥ ዋነኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ደራሲ ራሱ እግዚአብሔር ነው። እሱ ዓለምን መፍጠርና መምራት ብቻ ሳይሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምናገኘውን የፍጥረታትና የደኅንነት ታሪክ እንዲጻፍ አደረገ። እሱ ሰዎችን እንደ ደራሲዎች በመምረጥ መለኮታዊ የሆኑ ድርጊቶችን በሰዎች ቃላት እንዲያሰፍሩና ይህንንም በተሳካ ሁኔታ ያከናውኑ ዘንድ ደራሲዎቹ የየራሳቸውን ግላዊ ክህሎት፣ የአጻጻፍ ዘይቤና እውቀት እንዲጠቀሙ አደረገ። ለደራሲነት የተመረጡት ሰዎች ቢሆኑም ቅሉ መግለጥ የፈለገውን ሁሉ ይገልጥ ዘንድ በነርሱ ውስጥ እግዚአብሔር ሠራ።


መጽሐፍ ቅዱስን ምን ያህል ሰዎች እንደጻፉት የሚያውቅ ማንም የለም። አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፎች ለምሳሌ የቅዱስ ጳውሎስ መልእክቶች ሙሉ ለሙሉ የአንድ ጸሐፊ ሥራ ሲሆኑ ሌሎች እንደ መዝሙረ ዳዊት፣ መጽሐፈ ምሳሌን የመሳሰሉት የብዙ ጸሐፊዎች ስብስብ ሥራ ናቸው። ከነዚህም ጸሐፊዎች ውስጥ አንዳንዶቹ ብቻ ተጠቅሰው ይገኛሉ። አብዛኞቹን የታሪክ መጻሕፍት ስንመለከት ደግሞ በአንድ ወይም በብዙ አርታዒዎች ማለትም ጽሑፎችን አሰባስበው እርማት በማድረግ ወጥ የሆነ ፍሰት እንዲኖረው በሚያደርጉ ሰዎች የተለያዩ የድሮ ምንጮችን በመጠቀም የጻፏቸው ናቸው። ለምሳሌም የመጽሐፈ ነገሥታት ጸሐፊ ብዙ ጊዜ “የእስራኤል ነገሥታት የታሪክ ዜና መዋዕል” እያለ እንደ ምንጭ የተጠቀመበትን ይጠቅሳል።


በአዲስ ኪዳን የምናገኛቸው አንዳንድ መልእክታት በመግቢያቸው ላይ ማን እንደጻፋቸው ይነግሩናል፤ አንዳንድ ነቢያትም የመጽሐፉ ደራሲ ራሳቸው እንደሆኑ ይገልጻሉ። ከዚያ ውጭ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፎች አልቦ ስም ናቸው፤ ማለትም መጽሐፎቹ ራሳቸው ጸሐፊያቸውን አይገልጹም። ስለዚህም ይህን ለማወቅ በትውፊትና በተደረጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንታዊ ጥናቶች መመርኮዛችን የግድ ነው። ለምሳሌም ያህል ሙሴ አምስቱን የሕግ (ኦሪት) መጽሐፍት፤ ሐዋርያው ዮሐንስም የራእይን መጽሐፍ እንደጻፈ ትውፊት ይነግረናል።


የዘመናችን የመጽሐፍ ቅዱስ ተመራማሪዎች በበኩላቸው የእያንዳንዱን መጽሐፍ ጸሐፊ ለማወቅ አሥርት ዓመታትን የሚያልፍ ጥናት ያካሂዳሉ። በርግጥ ሙሴ አምስቱን የኦሪት መጽሐፍት ጻፋቸው ወይስ አራት የተለያዩ ቀደምት ሰነዶች በአንድነት ተቀመጡ? ወይስ ከአፈ ታሪክ ከጊዜ በኋላ በጽሑፍ የተቀመጡ መጻሕፍት ናቸው? የዮሐንስ ራእይ ጸሐፊስ ራሱ ሐዋርያው ዮሐንስ ነው ወይስ ስመ ሞክሼ አንድ ሌላ ክርስቲያን? ይህንና መሰል ጥያቄዎች በርግጥ በመስኩ ለሚመራመሩ ሊቃውንት ትኩረት የሚስቡ ቢሆንም ለአብዛኛው የመጽሐፍ ቅዱስ አንባቢ ክርስቲያን ግን አንገብጋቢና መሠረታዊ ጥያቄዎች አይደሉም።


ዋና ማስታወስ ያለብን ቁምነገር የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት በሙሉ በእግዚአብሔር አነሣሽነት የተጻፉ የደኅንነት መጻሕፍት መሆናቸውን ነው። ግምታዊ የሆኑ የመጻሕፍት ምንጮች ሙሉ ለሙሉ የምንተማመንባቸው ጽሑፋት አይደሉም፤ በርግጥ መጽሐፎቹ እንዴት እንደተጻፉ የበለጠ ባወቅን ቁጥር ይበልጥ መልእክታቸውን ለመረዳት ያግዘናል። ሆኖም ግን የመጽሐፍ ቅዱስ ዋነኛ ደራሲ እግዚአብሔር እንጂ በሃሳቦች የምናዋቅረው ዓይነት ተራ መጽሐፍ ያለመሆኑን መዘንጋት አይገባንም።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት - ብሉይና አዲስ ኪዳናት 

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት