Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የኩፔርቲኖው ቅ. ዮሴፍ - መስከረም 8

የኩፔርቲኖው ቅ. ዮሴፍ

Joseph Cupertinoመስከረም 8 - ቅ. ዮሴፍ ዘኩፔርቲኖ የትውልድ አገሩ ጣልያን ሲሆን፤ የኖረውም ከ1603-1663 ዓ.ም. ነው። እሱን ዝነኛ ያደረገው በጸሎት ጊዜ በአየር ላይ በመንሳፈፉ ነው። ገና በልጅነቱ ለጸሎት ያለውን ፍቅር አሳይቷል። ከካፑቺኒ ወንድሞች ጋር ጥቂት የሙያ ጊዜያቶች  ካሳለፈ በኋላ የፍራንቼስካውያን ገዳማዊ ሕይወት ተቀላቅሏል። ለአጭር ጊዜ የገዳሙን በቅሎዎች የመንከባከብ ኃላፊነትን ከጨረሰ በኋላ ለክህነት የሚያዘጋጀው ትምህርቱን ጀምሯል። ጥናቱ በጣም ቢከብደውም ዮሴፍ ባለው በጸሎት ሕይወቱ ብዙ ጥቅም አግኝቶ ክህነቱን በ1628 ዓ.ም. ተቀብሏል።

           የዮሴፍ በጸሎት ጊዜ በአየር ላይ የመንሳፈፍ ሁኔታ እንደ በሆነ መልኩ ፈተና እየሆነ መጥቶ ነበር፤ ምክንያቱም አንዳንድ ሰዎች ልክ ወደ ሰርከስ ትርኢት እንደሚሔድ እየመጡ ይመለከቱት ነበር። ይህ ስጦታ ዮሴፍን ትሕትና፣ ትእግስተኛና ታዛዥ አድርጎታል። አልፎ አልፎ እግዚአብሔር የረሳው ቢመስለውም በአብዛኛው የሕይወቱን ጊዜ ያሳለፈው ራሱን በሰንሰለት በማሰርና በመጾም ነበር። የገዳሙ መነኮሳትም ለዮሴፍና ለማሕበሩ ደህንነት ሲባል ብዙ ጊዜ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታዎች የምደባ ቅያሪ አድርገው ነበር። ከተፈጥሮ ሕግ በላይ የሆነ የሚታይበት በጸሎት ጊዜ ከምድር ከፍ ብሎ የመንሳፈፍ ሁኔታው ለምርምርም ቀርቦ መርማሪዎቹ የሚፈልጉትን ከጠየቁት በኋላ ከጥርጣሬ ነጻ ሆነው በነፃ ለቀውታል።

           ዮሴፍ በ1767 ዓ.ም. ቅድስናው ታወጀ። ቅድስናው ከመታወጁ በፊት በተደረገው የጥናት ሂደት ውስጥ 70 ጊዜ የሚሆን በጸሎት ጊዜ የአየር ላይ መንሳፈፍ ሁኔታ እንዳደረገ ተመዝግቧል።

ትርጉም፦ ዮሴፍ ወልደዮሐንስ

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።