እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የመልእክቶቹ ቅደም ተከተል፣ የተጻፈበት ዓመት - ቦታ - ዋና ይዘቱ

. የመልእክቶቹ ቅደም ተከተል

         ይህ ቅደም ተከትል በሦስት የተከፋፈለ ነው። መጀመርያው ዓምድ ቀኖናዊ ቅደም ተከተል ማለትም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በ4ኛው ክ.ዘ. መጨረሻ አካባቢ ሲካተቱ መልእክቶቹ የተሰጣቸውና ዛሬም የምናገኘው ቅደም ተከተል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የትሬንቶ ጉባኤ በ1546 ዓ.ም. ያጸደቀው እንዲሁም ሦስተኛው ደግሞ የክርስትና ትውፊት ይከተለው የነበረው ቅደም ተከትል ነው። በአሁኑም ዘመን የምንጠቀምበት መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን ቅደም ተከትል የተከተለ ነው። በዚህም ምክንያትቀኖናዊ” - ለሁሉም ማነጻጸሪያ የሚሆን መመዘኛ ተባለ። ሁለተኛው ዓምድ የተጻፈበትን ግዜ እንደ ቅደም ተከተሉ ተቀምጧል፤ ሦስተኛው ደግሞ የተጻፈበትን ቦታ - ማለት ከአንድ ከተማ ወይም ቦታ የተላኩትን ለማመልከት በአንድ ላይ ማለት ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምናገኘው (ቀኖናዊ) ቅደም ተከትል

በተጻፈበት ዓመተ ምሕረት ቅደም ተከተል መሠረት

የተጻፈበት ቦታ

ቍ.

መልእክት

ዓመት

ቦታ

መልእክት

ዓመት

መልእክት

ቦታ

1

ሮሜ

57/58

ቆሮንቶስ

1 ተሰሎንቄ

51

1 ተሰሎንቄ

 

ከ ቆሮንቶስ

2

1 ቆሮንቶስ

57

ኤፌሶን

2 ተሰሎንቄ

51

2 ተሰሎንቄ

3

2 ቆሮንቶስ

57

መቄዶንያ

1 ቆሮንቶስ

56

ገላትያ

4

ገላትያ

57

ኤፌሶን

ገላትያ

56

ሮሜ

5

ኤፊሶን

61-63

ሮማ

2 ቆሮንቶስ

57

 

 

ከ ኤፌሶን

6

ፊልጵስዩስ

61-63

ሮማ(ኤፌሶን)

1 ቆሮንቶስ

57

1 ቆሮንቶስ

7

ቆላስያስ

61-63

ሮማ

ገላትያ/2 ቆሮ.

56/57

2 ቆሮንቶስ

8

1 ተሰሎንቄ

51-

ቆሮንቶስ

ሮሜ

57/58

ፊልጵስዩስ?

9

2 ተሰሎንቄ

51-

ቆሮንቶስ

ኤፌሶን - ፊልጵስዩስ

62

63

 

 

 

ሮሜ

10

1 ጢሞቴዎስ

65

መቄዶንያ

ፊልጵስዩስ

57

ቆላስያስ

11

2 ጢሞቴዎስ

67

ሮማ

ቆላስያስ

62

ኤፌሶን

12

ቲቶ

65-

መቄዶንያ

ፊልሞና

62

ፊልሞና

13

ፊልሞና

61-63

ሮማ

ቲቶ

66

1 ጢሞቴዎስ

14

ዕብራውያን

67

 

1 ጢሞቴዎስ

2 ጢሞቴዎስ

ዕብራውያን

66

66

67

2 ጢሞቴዎስ

ቲቶ

ፊልጵስዩስ?

 

የተጻፈበት ዓመት - ቦታ - ዋና ይዘቱ 

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምናገኘው (ቀኖናዊ) ቅደም ተከትል

 የተጻፈበት ዓመት

የተጻፈበት ቦታ

ዋና ይዘቱ

 

1

ሮሜ

57/58

ቆሮንቶስ

ስለ ድኅነት ያስተምራል፤ በዝርዝር ያስረዳል

 

2

1 ቆሮንቶስ

57

ኤፌሶን

ስለ ተለያየ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

 

3

2 ቆሮንቶስ

57

መቄዶንያ

ክርስቲያናዊ አገልግሎት እንዴት መሆን እንዳለበት

 

4

ገላትያ

57

ኤፌሶን

መዳን በእምነት የሚልና ፍሬዎቹን ይተነትናል

 

5

ኤፊሶን

61-63

ሮማ

አማኙ “በክርስቶስ” ያለው ቦታ

 

6

ፊልጵስዩስ

61-63

ሮማ(ኤፌሶን)

በክርስቶስ የሚያምነው አመለካከቱ

 

7

ቆላስያስ

61-63

ሮማ

አማኝ በክርስቶስ ምልአትን ያገኛል

 

8

1 ተሰሎንቄ

51-

ቆሮንቶስ

ስለ ክርስቶስ ሁለተኛ መምጣት ይናገራል

 

9

2 ተሰሎንቄ

51-

ቆሮንቶስ

ስለ ክርስቶስ ሁለተኛ መምጣት ግልጽ ያደርግዋል

 

10

1 ጢሞቴዎስ

65

መቄዶንያ

አገልጋይ/መሪ ማድረግ ያለበት

 

11

2 ጢሞቴዎስ

67

ሮማ

ለትንሹ መሪ/አገልጋይ የመጨረሻ አደራ

 

12

ቲቶ

65-

መቄዶንያ

እውነተኛ ትምህርትና የመሪው ሥነ ምግባር

 

13

ፊልሞና

61-63

ሮማ

ጳውሎስ አንድ ነገር እንዲደረግለት ይጠይቃል

 

14

ዕብራውያን

67

 

የክርስቶስ የክርስቲያናዊ ሕይወት ትልቅነት

 

 መልእክቶቹ በየክፍላቸው ሲመደቡ

 . ትልልቅ መልእክቶች (ከፊልጵስዩስ ጋር ሰባቱ ትልልቅ መልእክቶች ተብለው ይጠራሉ።)

1.   1 ተሰሎንቄ

2.   2 ተሰሎንቄ

3.   1 ቆሮንቶስ

4.   2 ቆሮንቶስ

5.   ገላትያ

6.   ሮማ

7.   ፊልጵስዩስ

. የእስር ቤት መልእክቶች (ጳውሎስ ታስሮ እያለ የጻፋቸው መልእክቶች)

1.   ፊልጵስዩስ

2.   ፊልሞና

3.   ቆላስያስ

4.   ኤፌሶን

. ሓዋርያዊ/ እረኛዊ መልእክቶች

1.   1 ጢሞቴዎስ - በኤፌሶን መሪ የነበረ

2.   ቲቶ - በቀርጤስ መሪ የነበረ

3.   2 ጢሞቴዎስ - በኤፌሶን መሪ የነበረ

4.   ዕብራውያን

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት - ብሉይና አዲስ ኪዳናት 

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት