4- የትኞቹ መጽሐፍ የመጽሐፍ ቅዱስ አካል እንደሆኑ በምን እናውቃለን?
- Category: መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት - ባጭሩ
- Published: Friday, 12 April 2013 19:13
- Written by Super User
- Hits: 3811
- 12 Apr
4. የትኞቹ መጽሐፍ የመጽሐፍ ቅዱስ አካል እነደሆኑ በምን እናውቃለን?
የተለያዩ አሳታሚዎች ጥንታዊ ጽሑፎችን ከፊታችን በማቅረብ የተረሱ የወንጌል ተግባራትን እንደያዙ የኢየሱስን ቀሪ ሥራዎች እንደሚዘክሩ እውነተኛ መጽሐፍት አድርገው በሚያቀርቡበት ዓለማችን ውስጥ የምንሰማው ተደጋጋሚ ጥያቄ ነው፡፡ የቶማስ ወንጌል፣ የይሁዳ ወንጌል፣ የፊልጶስ ወንጌል፣ የሚባሉትን ጥንታዊ መጽሐፍት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተካተቱትን ለምንድነው? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መካተት ያለበትን እና መካተት የሌለበትን የሚወስነው ማነው?
ሐዋርያት መጽሐፍ ቅዱስን እንደ ቅዱስ ትውፊት አካል እና እንደ እምነት አድርገው ለቤተክርስቲያን አደራ ሰጥተዋል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን በመንፈስ ቅድስ መሪነት እነዚህን ጽሑፎች በመደበኛው ዝርዝር ለማዋቀር ያለውን አስፈላጊነት ተረዳች፡፡ ይህ የተሟላ የመጽሐፍት ዝርዝር የቅዱሳን መጽሐፍት "ቀኖና" ይባላል፡፡
ቀኖና የሚለው የግሪክ ቃል "ማስመሪያ፣ መለኪያ፣ መሸለጊያ ወይም መመተሪያ" የሚሉትን ትርጉሞች ያሰማል።
በመጀመርያ ጳጳሳት የመጽሐፍቱን ዝርዝር ያዋቀሩት በሃገረ ስብከታቸው ለሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ግልጋሎት ነበር፡፡ እንደ ዛሬው የማተሚያ ማሽን ባለማመኖሩ አብዛኞቹ አብያተ ክርስቲያናት እና ምዕመናን ሙሉ "መጽሐፍ ቅዱስ" አልነበራቸውም፡፡ መጽሐፍት የሚባዙት እጅግ አድካሚ በሆነው በእጅ የመገልበጥ ሥራ ነበር፤ በዚህም የተነሳ መጽሐፍቱ ዋጋቸው የማይቀመስ እና በጣም ጥቂት ብቻ ነበሩ፤ ከዚህ አንፃር በግል መንፈሳዊነት ንባብ ማድረግ በጥቂት ክርስቲያኖች እጅ ብቻ የሚገኝ ቅንጦት ነበር፡፡ ምእመናን መጽሐፍ ቅዱስን የሚያገኙት በመሥዋዕተ ቅደሴ ውስጥ ሲነበብ በማድመጥ ነበር፡፡ ጥንታዊው ቀኖና በቅዳሴ ላይ ሊነበቡ የሚችሉ መጽሐፍትን ያካተተ ብቻ ነበር፡፡
አልፎ አልፎ ለሚነሱ እንግዳ ይዘት ያላቸው የስህተት "ወንጌላት"ን ለመቃወም ጳጳሳት የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖናን ለማዋቀር ይነሳሱ ነበር፡፡ እነዚህ የተሳሳቱ መጽሐፍት በአንዳንድ የኢየሱስ ሐዋርያት ስም የቀረቡ በመሆናቸው ማጣራት ያስፈልግ ነበር፡፡ ለምሳሌ የአንጾኪያው የመጀመርያ ጳጳስ በጊዜው ይዘወተር የነበረውን "የጴጥሮስ ወንጌል" የሚል መጽሐፍ እንዳይጠቀሙ በእርሱ ሃገረ ስብከት ሥር ያሉትን አብያተ ክርስቲያናት በግልጽ አግዷቸዋል፡፡
ከእነዚህ መጽሐፍት አብዛኞቹ ዛሬም በአርኪዮሎጂ እና በታሪክ አጥኚዎች አማካኝነት በኛ ዘንድ በአዲስ መልክ ብቅ ብለዋል፡፡ ሊቃውንት እና የቤተክርስቲያን ወገኖች "አፖክሊፋ" ብለው ይጠራቸዋል፤ በግሪኩ ስያሜ "የተደበቁ" ማለት ሲሆን የዚህ ምክንያት እነዚህ መጽሐፍት በቤተ ክርስቲያን ዘንድ ተቀባይነት በማጣታቸው ነው፡፡ የመገናኛ ብዙኅን ያለ እረፍት የሚያሞካሿቸው ቢሆኑም ተአማኒነት የጐደላቸው ጽሑፎች ናቸው፤ ብዙዎቹ ጽሑፎች ወንጌል ከተፃፈ ከረጅም ጊዜ በኋላ የተፃፉ፣ በይዘታቸው ወጥ ወይም ቀጥ ያለ ዘውግ ያላቸው እና ለተራ ንባብ የተፃፉ ናቸው፡፡ እነዚህ በቤተክርስቲያን ሕጋዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና ውስጥ ያልተካተቱባቸው አያሌ አሳማኝ ምክኒያቶች አሉ፡፡
የተለያዩ የቀኖና ዝርዝሮች ከጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያዎቹ ክፍል ዘመናት እንስቶ ቀርበዋል፡፡ በ367 ዓ.ም ቅዱስ አቴናሲዮስ የአዲስ ኪዳን የቀኖና መጽሐፍት ልክ ዛሬ ያሉትን ዓይነት እንደሆኑ አረጋግጧል፡፡ የተለያዩ ጳጳሳት በሂፖ ጉባኤ /393 ዓ.ም/ እና በካርቴጅ ጉባኤ /በ397 ዓ.ም/ ላይ ይህንኑ የቀኖና ዝርዝር አጽድቀዋል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍት የመጨረሻው የቀኖና ዝርዝር የጸደቀው በአራተኛው ክፍለ ዘመን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሮም በጠሩት ጉባኤ ላይ ነው፡፡
ነገር ግን ደግመው የምንመሰክረው ነገር ቢኖር እነዚህ የተለያዩ ጉባኤያት ያጸደቁት ነገር አስቀድመሞ ከሐዋርያት እጅ በአደራ የተቀበሉትን እና በቤተ ክርስቲያን የተቀደሰው ትውፊት ጠብቆ ያቆየላቸውን ልማድና እምነት ነው፡፡