እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

4.2. - የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት

4.2. - የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት

ለመጀመርያዎቹ ክርስቲያኖች "መጽሐፍ ቅዱስ" ማለት ዛሬ እኛ ብሉይ ኪዳን ብለን የምንጠራው ነው፡፡ ለመጀመርያዎቹ ዘመናት በተለይም ክርስትና በኢየሩሳሌም ማዕከሉን ባደረገበት ወቅት በእርግጥም ከዚህ በላይ መፃፍ አያስፈልግም ነበር፡፡ ሐዋርያትም በሚሰብኩበት ጊዜ ከኢየሱስ ሞት፣ ትንሳኤ እና መለኮታዊ ክብር አንፃር የሕግ እና የነቢያንት መጽሐፍት እየጠቀሱ ይተረጉሙ ነበር፡፡ ነገር ግን በጣም በአጭር ጊዜ ክርስትና በፍልስጤም እና በመላው የሮም ግዛቶች ከዚያም ባሻገር ባሉ ቦታዎች ሁሉ ተስፋፋ፡፡ አሁን እንግዲህ ሐዋርያት በአንድ ጊዜ ሁሉም ቦታ ደርሰው መስበክ የማይቻላቸው ሆነ፡፡

ስለዚህ ሐዋርያት የመረጧቸውን አብያተ ክርስቲያናት ለማበረታታት፣ ግጭቶችና አለመግባባቶችን ለመፍታት እና አንዳንድ ጥያቄ አዘል ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እውነተኛውን የክርስቶስን ትምህርት ለመግለጥ በተደጋጋሚ የጽሑፍ መልእክት መላክ ጀመሩ፡፡ እነዚህ የኢየሱሱ እንደራሴ የሆኑት ሐዋርያት መልእክቶች የክርስቲያን ማኅበር ለአምልኮ በሚሰበስቡበት ወቅት እንደ አዋጅ ይነበቡ ጀመር፡፡ እነዚህ መልእክቶች ሐዋርያት በቶሎ በግንባር ለመገኘት ባልቻሉባቸው ሥፍራዎች ለሚገኙ ማኅበራት የተላኩ የመጀመርያዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ሐዋርያዊ መልእክቶች ሆኑ፡፡

በተመሳሳይ ምክኒያት እየሰፋ የመጣው የቤተክርስቲያን ማኅበር ስለ ኢየሱስ ሕይወት የሚያትቱ ጽሑፎች እያስፈለጉት መጡ፡፡ በቦታው ተገኝተው ኢየሱስን በአካል ላገኙት እና ያደረገውንም የሆነውን ነገር ለተመለከቱት ክርስቲያኖች መጽሐፍ አያስፈልጋቸውም፤ ለቀባሪ አረዱት እንደሚባለው፡፡ ነገር ግን አሁን ሰለ ክርስቶስ ሕይወት ሰምተው እና በቦታው ተገኝተው ከእርሱ ጋር ከነበሩት አማኞች ቁጥር ይልቅ የዚህ ተቃራኒ የሆኑት ክርስቲያኖች ቁጥር ይበልጥ ጨመረ፡፡ የኢሱስን ሐዋርያዊ ሥራ ለማስተላለፍ እርግጠኛነት ሲባል የቤተ ክርስቲያን ማኅበር ለአምልኮ ሲሰበሰብ ታሪኩ በቃል ይተረክ ነበር፤ ይህን ተመርኩዘው ስለ እርሱ የተሻለ የመረጃ አቅም ወይም ግብአት የነበራቸው ግለሰቦች በዓይናቸው ያዩትን ነገር በ "ወንጌል" ውስጥ በጽሑፍ ማስፈር ጀመሩ፡፡ መንጌል የምሥራች ታሪክ ነው፡፡

ነገር ግን በክርስቲያኖች ሥርዐተ አምልኮ ውስጥ የሚነበቡት የሐዋርያትን እውነተኛ ምሥክርነቶች የያዙት ትክክለኛ መልእክቶች እና በምድር ላይ የነበረውን እውነተኛውን የክርስቶስን ሕይወት የሚመሰክሩ መንጌላት ብቻ ሆኑ፡፡ ሆኖም ግን ከአዲስ ኪዳን መጠናቀቅ በኋላ እንኳን አያሌ መጽሐፍት ተጽፈዋል፤ በሉቃስ ወንጌል 1፡1 ላይ እንደምንመለከተው ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን በመፃፍ ብዕሩን ከመጨበጡ አስቀድሞ የኢየሱስ ሕይወት በብዙ ጸሐፊያን እንደተፃፈ ይነግረናል፡፡

ዛሬ ግን መቶ ሠነዶችን ወይ የመጽሐፍ ጥራዞችን ሰብስቦ የትኞቹ እውተኞች የመሆናቸውን ጉዳይ የማጣራት ሥራ ያበቃለት ይመስላል፡፡ ነገር ግን አስቀድሞ ሥራው በተፈጸመበት ወቅት ያለቀለት ተሥፋ ቢስ ነገር አልነበረሙ፡፡ ቤተ ክርስቲያን እነዚህን መጽሐፍት የወሰነችው ሐዋርያት በሕይወት ሳሉ ነበር፡፡ ኢየሱስ በጣም ዝነኛ ሰባኪ ስለነበር በሺዎች የሚቆጠሩ ሕዝቦች ቢያንስ ግማሽ ያክሉን ሕይወቱንና ሥራውን ለማየት ችለዋል፡፡ እንደ ጴጥሮስ እና ጳውሎስ ያሉ ሐዋርያት በጣም በብዙ ሀገሮች በመዘዋወር ሺዎችን በጊዜያቸው አስተምረዋል፡፡ ኢየሱስ እና ሐዋርያቱ የተናገሩትን እና ያደረጉትን ነገር ሁሉ የሚያረጋግጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን የዓይን ምሥክሮች ነበሩ፡፡

በሁለተኛው ክፍለ ዘመን አጋማሺ አካባቢ ሐዋርያት ሲያስተምሩ በጆሮአቸው የሰሙ ሰዎች በሕይወት እያሉ የመጽሐፍቱ ዝርዝር መልክ መልክ ይዞ ነበር፡፡ የሞራቱራውያን ቀኖና በመቶዎቹ ማለቂያ አካባቢ ተጽፎ ያለቀ ሲሆን በጊዜው የነበረው የመጽሐፍት ዘርዝር አዲስ ኪዳን ዛሬ እኛ ካለን መጽሐፍቶች ጋር ከሞላ ጎደል የሚመሳሰል ነበር፡፡

ከዚህ በኋላ የተጠሩት የተለያዩ የቤተ ክርስቲያን ጉባኤያት የክርስቲያን የመጽሐፍት ቀኖናን፣ አዲስ ኪዳንን እና ብሉይ ኪዳንን በተገቢ መልኩ ከፋፍለው አዋቀሯቸው፡፡ የደዮትሮካኖኒካል መጽሐፍትን አንቀበልም ላሉት የኘሮቴስታንት ክርስቲያኖች ምላሽ ለመስጠት ሲባል የትሬንቶ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያን ሥልጣን መሠረት የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍትን ዝርዝር አወጀ፡፡ ነገር ግን ይህ የመጽሐፍት ቀኖና የተሻሻለ ፈጠራ አልነበረም፤ አስቀድሞ በቤተክርስቲያን ዘንድ የጋራ መግባባት የተደረሰበት ነበር፡፡ የጉባኤያቱ ተግባር የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት እና ተግባር የነበረውን እምነት ማስቀጠል እና እውነተኛነቱን እንዳይበረዝ መከላከል ነው፡፡

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት - ብሉይና አዲስ ኪዳናት 

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት