Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የምንኩስና መሐላ በቅ. ዮሴፍ ዘሲታውያን

4እሑድ ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ወንድም ፍቃደ ሥላሴ (ፍቃዱ) ተስፋዬ እና ወንድም ሉቃስ (ብርሃኑ) ቡናሮ በአዲስ አበባ ቅ. ዮሴፍ ገዳም ዘሲታውያን የመጨረሻ የምንኩስና መሐላቸውን አድርገዋል። ወንድም ፍቃደ ሥላሴ የመንዲዳ መድኃኔዓለም ቁምስና እንዲሁም ወንድም ሉቃስ የዳውሮ ቅ. ፍልሠታ ለማርያም ቁምስና ፍሬዎች ናቸው። ሁለቱ ወንድሞች በአሁኑ ሰዓት የነገረ መለኮት የመጨረሻ ዓመት ተማሪዎች ሲሆኑ፤ ከእነርሱ ጋር በጠቅላላው ዘጠኝ በሕንጸት ላይ የሚገኙ የዓቢይ ዘርአ ምንኩስና የማኅበሩ ተማሪዎች በአዲስ አበባ ቅ. ዮሴፍ ገዳም ይገኛሉ።

በኢትዮጵያ የገዳመ ሲታውያን ኃላፊ በሆኑት በአባ ዳንኤል ጌታቸው በተመራው መሥዋዕተ ቅዳሴ ከሲታውያን አባቶች ጋር ከላዛሪስት፣ ከካፑቺን እንዲሁም ከተለያዩ ሀገረ ስብከቶች ካህናት ተሳትፈዋል። በነበረው የስብከት ጊዜ አባ ዳንኤል ሰው ለአምላክ ሊሰጠው የሚችለው ትልቁ የፍቅር መገለጫ ራስን መስጠት መሆኑን ገልጸው፣ በወንጌል ክርስቶስ ያወደሳት ድኻዋ መበለትም በሙዳየ ምጽዋት ውስጥ ለአምላክ ብላ የሰጠችው የተረፋትን ነገር ሳይሆን ያላትን ነገር ሁሉ፣ ኑሮዋንም ሁሉ እንደሆነ አስታውሰዋል። ስለዚህም በእለቱ የመጨረሻ መሓላቸውን ያደረጉትን ሁለቱን ወጣቶች ራሳቸውን ለአምላክ በመስጠታቸው አመስግነው፣ እነሱንም ለእግዚአብሔር አገልግሎት ለቤተ ክርስቲያን የሰጡ ወላጆቻቸውንም አመስግነዋል።

በዕለቱ የተለያዩ ማኅበራት ደናግል እህቶች፣ ቁጥራቸው ብዙ የሆነ ምእመናን ተገኝተዋል። በመጨረሻም ገዳሙ ባዘጋጀው የምሳ ዝግጅት ላይ የተጋበዙ ሁሉ ተገኝተው፤ ዕለቱ ታላቅ የምስጋና ቀን ሆኖ ውሏል።

5

6

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።