እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ልጅ የእግዚአብሔር ስጦታ ስለመሆኑ

ልጅ የእግዚአብሔር ስጦታ ስለመሆኑ

ቅዱስ መጽሐፍና የቤተ ክርስቲያን ትውፊት በቤተሰብ ውስጥ የልጆች መበርከት የእግዚአብሔር ቡራኬና የወደጆች ለጋስነት ምልክት ነው ይላሉ፡፡

መሀን መሆናቸውን የተረዱ ባልና ሚስት እጅግ ይሳቀቃሉ፡፡ አብርሃምም “አቤት እግዚአብሔር ሆይ ምን ትሰጠኛለህ? እኔም ያለ ልጅ እሄዳለሁ” ዘፍ. 15፡2 ሲል ጠየቀው፡፡ ራሔልም ለባሏ ለያዕቆብ “ልጅ ስጠኝ፤ ይህስ ካልሆነ እሞታለሁ” ብላዋለች፡፡

ሰብአዊ መሀንነትን ለመቀነስ የሚከናወን የሳይንሳዊ ጥናት “ሰውን፣ የማይገሠሡ መብቶቹንና እንዲሁም በእግዚአብሔር ዕቅድና ፈቃድ መሠረት እውነተኛና ምሉዕ በጐነቱን የሚያገለግልና የሚያራምድ ከሆነ ተገቢ ድጋፍ ሊደረግለት ይገባል፡፡”

ከጥንዱ ውጭ ሌላን ሰው ጣልቃ በማስገባት /የወንድ ዘር ወይም ዕንቁላል፣ ሞግዚት ማህፀን/ የባልና የሚስትን መለያየት የሚያስከትሉ ቴክኒኮችን መጠቀም ሥነ ምግባር የጐደለው ሥራ ነው፡፡ እነዚህ ቴክኒኮች /ሰው ሰራሽ የማዳቀልና የጽንስ ሥራ/ ልጅ ከሚያውቃቸው በጋብቻ ኪዳን ከተጣመሩ አባትና እናት የመወለድ መብትን እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡ እነዚህ ዘዴዎች ባልና ሚስት አንዱ በሌላው አማካይነት ብቻ “አባትና እናት የመሆን መብት” እንዳያገኙ ያደርጋል፡፡

ባልና ሚስቱን ብቻ የሚያሳትፉ ቴክኒኮች ምናልባት አለ መጠን አስከፊ ባይሆኑም  በሥነ ምግባር በኩል ተቀባይነት የላቸውም፡፡ እነዚህ ዘዴዎች ሩካቤን ከማፍራት ሥራውን ይነጥሉታል፡፡ ልጁን ወደዚህ ዓለም የሚያመጣው ድርጊት ሁለት ሰዎች አርስ በእርስ በመሰጣጠት የሚያደርጉት መሆኑ ቀርቶ “የሽሉን ማንነትና ሕይወት ለሥነ-ሕይወት ጠበብትና ለሐኪሞች ኃላፊነት የሚተው በሰው ልጅ መገኛና ዕጣም ላይ የቴክኖሎጂን የበላይነት የሚያሰፍን ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት የበላይነት የሰፈነበት ግኑኝነት በራሱ ለወላጆችና ለልጆች ክብርና እኩልነት ተፃራሪ ነው፡፡” “በሥነ-ምግባራዊ ገጽታን አኳም ሲታይ ዘር ማፍራት የጋብቻዊው ፍቅር ውጤት ማለትም የጥንዶቹ አንድነት የተለየ እንቅስቃሴ ውጤት እንዲሆን ባልተፈለገ ጊዜ ፍጽምናውን ያጣል፡፡ ዘር ማፍራት ከሰው ክብር ጋር በተጣጣመ መልኩ እውን እንዲሆን ማድረግ የሚቻለው ለጋብቻዊ ሩካቤና ለሚሰጡት ትርጉሞች ትስስር በሚኖር አክብሮት ለሰው ልጅ አንድነት በሚሰጥ ክብር ብቻ ነው፡፡”

ልጅ አንድ ሰው ይገባኛል የሚለው ነገር ሳይሆን ስጦታ ነው፤ “የአንድ ጋብቻ የላቀ ስጦታ” ልጅ ነው፡፡ “የልጅ ባለቤትነት መብት” የሚለውን አባባል ሊጠቁም እንደሚችለው ልጅ እንደ ንብረት ሊቆጠር አይገባውም፡፡ በዚህ ዙሪያ ትክከለኛ መብቆች ያሉት ልጁ ብቻ ነው፤ ይህም “የወላጆቹ ልዩ የጋብቻዊ ሩካቤ ፍሬ” የመሆን መብትና “በተፀነሰበት ወቅት ጀምሮ እንደ ሰው የመከበር መብት” ነው፡፡

ሥጋዊ መሀንነት ፍጹም ክፋት አለመሆኑን ወንጌል ያመለክታል፡፡ ሕጋዊ የሕክምና አገልግሎቶችን ሁሉ ከሞከሩ በኋላም በመሐንነት የሚሰቃዩ ባልና ሚስት የመንፈሳዊ ልጆች ሁሉ ምንጭ ከሆነው ከጌታ መስቀል ጋር ራሳቸውን ማዋሐድ ይኖርባቸዋል፡፡ የተጣሉ ልጆችን በመሰብሰብ ወይም ለሌሎች አስፈላጊ አገልግሎቶችን በመስጠት ቸርነታቸውን መግለጽ ይችላል፡፡

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት