እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የካህን ዘለዓለማዊ ምርጫ

የካህን ዘለዓለማዊ ምርጫ

ልጄ ሆይ! አንተን ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣህ ያለ ምክንያት አይደለም፤ የክህነትንም ሥልጣን ያለበስህ ያለ ምክንያት አይደለም፡፡  አባቴ እኔ የሱ ካህን እንድሆን በወሰነ ጊዜ በዚያኑ ሰዓት አንተ የኔ አገልገይ እንድትሆን ወስኖሃል፡፡ ከዘለዓለመ ዓለም ጀምሮ በማይለወጥ ትእዛዝ ቦታህ ከኔ ቦታ አጠገብ ተወስኖ ስምህም በኔ እጅ ተጽፎ የካህናዊ ክብሬ ተካፋይ እንድትሆን ተመርጠሃል፡፡ መለኮታዊ አባቴ ከዘለዓለም ጀምሮ የሰውነት ባሕሪዬንና በመስቀል ላይ መሥዋዕት አድርጌ የማቀርበውን ሥጋ የምትሰጠኝ እናት እንድትኖረኝ ወሰነ፡፡ እንዲሁም አባቴ በዘለዓለማዊ ውሳኔው ካህናት እንዲኖሩኝ ፈለገ፡፡ እነርሱም ምሥጢራዊ ሕይወትን ለብዙዎች እንዲሰጡና በመንበረ ታቦት ላይ እንደገና ለአብ መሥዋዕት ሆኜ እንድቀርብ ያደርጉኝ ዘንድ ተወሰኑ፡፡

አዬ ስንት መተሳሰሪያዎች ናቸው አንተን ከእኔና ከእናቴ ጋር አሰረው የሚይዙ! እነዚህም መተሳሰሪያዎች የተፈጠሩት ባንተ ፈቃድ ወይም ባንተ ሥራ አይደሉም፡፡ እኔን የመረጥኸኝ አንተ አይደለህም አንተ ሂደህ ፍሬ እንድታፈራ የመረጥሁህና ካህን ያደረግሁህ እኔ ነኝ፡፡ አባቴ አስቀድሞ ካልሳበው ማንም ወደኔ አይመጣም እንደ አሮን በእግዚአብሔር የተጠራ ካልሆነ በቀር ማንም የክህነት ሥልጣን ሊኖረው አይችልም፡፡ ኢምንትነትህን ኃጢአቶችህንና ወሮታ ቢስነትህን ሳልመለከት ከሺ መካከል አንተን መረጥሁ፡፡ በመንገድ ላይ ከሚገኘው ጭቃ አንሥቼህ የሕዝቤ መሪዎች ከሆኑት ጋር አጠገቤ አስቀመጥሁህ፡፡

ልሞት አንድ ቀን ሲቀረኝ የክህነት ምስጢርን ስሠራ አንተን በተለይ አስቤሃለሁ፤ አንተ የኔ ካህን፣ የኔ ወዳጅ የሥራየ ተካፋይ መሆንህን ማሰቤ መከራን ለመቀበል አደፋፍሮኛል፡፡ ከመጨረሻ ራት በኋላ ስለ አርድእቶቼና በነሱም ቃል ስለሚያምኑት ሰዎች ሁሉ ጸሎት ባደረግሁ ጊዜ ዓይኖቼ በደስታ ባንተም ላይ ዓርፈዋል፡፡ ስላንተ በመጸለይም እነዚህን እጅግ ከፍ ያሉትን ሥራዎችህን አንድ ቀን ለመፈጸም እንድትበቃ ኃይል ታገኝ ዘንድ ጸሎት አድርጌልሃለሁ፡፡ በመስቀል ላይ ልሞት ሳጣጥር በእግሮቼ ሥር ታማኙን ረድእ አየሁ አንተም በሱ አማካኝነት እንደነበርህ ዓወቅሁ ስለዚህ አንተንና ክህነትህን እሷ እንድትጠብቅ በማለት አንተንም ከሱ ጋር ለእናቴ አደራ ሰጥቻታለሁ፡፡ ከሙታን ከተነሳሁ በኋላም በዓለም ላይ ከዳር እስከ ዳር ወንጌልን እንዲያስተምሩ ሐዋርያቶቼን ስልክ አንተም አንድ ቀን በቤተ ክርስቲያኔ የምትይዘውን ሥፍራ አስቀድሜ ወስኛለሁ፤ አሁን በአደራ የተሰጡህንም ነፍሶች አስቀድሜ አዘጋጅቼልሃለሁ፡፡

ልጄ ሆይ! አንተ እኔን ማወቅ በማትችልበት ሰዓት እኔ አንተን ወደድሁህ፤ በኔ አጠገብ ሆነህ ሥፍራህን ለመያዝ በምድር ላይ የምትታይበትን ቀን በትእግሥት እጠባበቅ ነበር፡፡ በእንዴት ያለ ታላቅ ጥንቃቄ በልቤ ውስጥ ነፍስህን ከነፍሴ ጋር የሚያስተሳስረውንና በምሥጢረ ክህነት አማካይነት ከኔ ጋር ፍጹም አንድነትህንም የሚያዘጋጀውን አጽዳቂ ጸጋ ያን ጊዜ መረጥሁ! ገና በሕፃንነትህ ጊዜ ከጓደኞችህ የምትለይበት ገና ምንም ነገር ሳይኖር ቅዱሳን መላእክቶቼ በትጋት ያለማቋረጥ እየተከታተሉ ይጠብቁህ ነበር፤ እኔ የመረጥሁህ መሆንህን በማወቃቸው በክብር ይከቡህ ነበር፤ የነፍስና የሥጋ አደጋዎችን ከአንተ ወዲያ ለማራቅ በጥንቃቄ ይተጉ ነበረ፤ የክህነት ምኞት በልብህ እንዲያድር በውስጣዊ ምክር ቀስ በቀስ ያዘጋጁህ ነበር፤ መቸም አንድ ጊዜ የኔ አገልጋይ እንድትሆን መርጨሃለሁና ምንም እንኳ ብትበድለኝም እነርሱ ስለአንተ ይጸልዩልህ ነበር፡፡

ክህነት በተቀበልክበት ቀን ከሌሎች ፍጡራን ሁሉ አንተን ለይቼህ ወደ ልቤ አስገባሁህ፡፡ በነፍስህ ገብቶ ባንተ ላይ አምላካዊ ማህተሙን ያተመውን የኔ የክህነቴ ማህተም ባንተ ላይ እንዲታተም የሚያደረገውን መንፈስ ቅዱስን ላክሁልህ፡፡  በሰማይ ሆነ በምድር የሥልጣን ተካፋዬ አደረግሁህ፤ በኔ ላይና በደሜ ባዳንኋቸው በጐች ላይም ሙሉ ስልጣን ሰጠሁህ፡፡ ያም ባንተ ላይ የታተመው ማህተም የማይደመሰስ ነው እግዚአብሔር ምሏል ቃሉንም አይለውጥም እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት አንተ ለዘለዓለም ካህን ነህ፡፡ ልጄ ሆይ! ሰለዚህ አንተ የኔ ነህ የመሥዋዕቴ አገልጋይ ነህ፤ ለኃጢአተኛ ሰው የምሕረቴ መሣሪያ ነህ፡፡ የኔ ካህን ነህ አንተ እንደራሴዬ ነህ፡፡ ባንተ ላይ ያለኝን ተስፋ በከንቱ አታስቀር፤ ለነፍስህ ውስጥ የተከማቸውን የወርቅ መዝገብ አታባክን፤ በሰጠሁህ ታላቅ ስልጣን ሳትጠቀምበት አትቅር፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ አንተ ሁል ጊዜ ከእኔ ጋር ሆነህ “ያባቴን ጉዳዮች መፈጸም ይገባኛል” ማለት አለብህ፡፡

ምንጭ፡- "የኢየሱስ መልእክት ለካህኑ" ከሚለው መጸሐፍ የተወሰደ

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት